Research indexJournal article
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የተፈፃሚነት ወሰን ከጊዜ አንፃር᎓- በፍርዶች ላይ የቀረበ ትችት
Adugna
National Academic Digital Repository of Ethiopia15 Mar 2022Open access
NobleIDark:/48914/w1/20260525/3EE5D4B5DOI10.20372/bdujol.v4i2.847
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የተፈፃሚነት ወሰን ከጊዜ አንፃር᎓- በፍርዶች ላይ የቀረበ ትችት
Adugna · National Academic Digital Repository of Ethiopia · 2022
NobleIDark:/48914/w1/20260525/3EE5D4B5DOI10.20372/bdujol.v4i2.847
Free to read at the publisher
You can read the abstract here, or the full text at the publisher.
Abstract
በተለይ ከውርስ አንጻር በቀድሞዎቹ የገጠር መሬት ሕጎች እና አሁን በስራ ላይ ባሉት ሕጎች መካከል ሰፊ ልዩነቶች አሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ የቀድሞዎቹ ሕጎች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 89/1989 ወይም አዋጅ ቁጥር 46/1992) ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ሳይናዘዝ የሞተ ሰው የገጠር መሬት ይዞታ በውርስ ሊተላለፍ የሚችለው እንዴት ነው? ወራሾች በወቅቱ ውርሱን ያልጠየቁ ሆኖ ነገር ግን አዋጆቹ ከተሻሩ በኋላ አሁን ስራ ላይ ባለው አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ደንብ ቁጥር 51/1999 መሠረት ክስ ቢያቀርቡ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን እልባት መስጠት ያለባቸው በየትኛው ሕግ መሰረት ነው? የሚሉ ጥያቄዎች አዘውትረው ይነሳሉ፡፡ በዚህ ረገድ በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከፍትሐብሔር ሕጉ የውርስ መከፈት ጽንሰ ሀሳብ በመነሳት የገጠር መሬት ውርስ የሚጠይቅ ሰው ባለይዞታው በሞተበት ዘመን ከሚኖረው አጠቃለይ የማውረስ መብት አንፃር እየታየ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ሆኖም የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅርቡ በሁለት ጉዳዮች ላይ የመሬት ባለይዞታው የሞተበት ጊዜ ግምት ውስጥ ሳይገባ ክርክሩ መታየት ያለበት አሁን ስራ ላይ ባሉት ሕጎች መሠረት ነው የሚል አስገዳጅ ትርጉምና ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ይህ ትርጉም ከሕጎች ተፈጻሚነት ወሰን አንፃር አከራካሪ ሆኗል፡፡